Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሕዝቅኤል 41:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 በኪሩቤልና በዘንባባ ዛፎች የተሠራ ነበር፤ በኪሩብና በኪሩብ መካከል የዘንባባ ዛፍ ነበረ፤ እያንዳንዱም ኪሩብ ሁለት ፊቶች ነበሩት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ኪሩቤልና የዘንባባ ዛፍ ተቀርጸውበት ነበር፤ የዘንባባ ዛፎቹ የተቀረጹት በኪሩብና በኪሩብ መካከል ነበር። እያንዳንዱም ኪሩብ ሁለት ፊት ነበረው፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 በመለበጃውም ላይ ያለው ቅርጽ የዘንባባ ዛፎችና የኪሩቤል ስዕል ነበር፤ በክፍሉም ዙሪያ የዘንባባና የኪሩቤል ሥዕሎች ተሰባጥረው ተስለውበታል፤ እያንዳንዱም ኪሩብ ሁለት ፊቶች ነበሩት፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ኪሩ​ቤ​ልና የዘ​ን​ባ​ባው ዛፎች ተቀ​ር​ጸ​ው​በት ነበር፤ የዘ​ን​ባ​ባ​ውም ዛፍ ከኪ​ሩ​ብና ከኪ​ሩብ መካ​ከል ነበረ፤ ለእ​ያ​ን​ዳ​ዱም ኪሩብ ሁለት ፊት ነበ​ረው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ኪሩቤልና የዘንባባው ዛፎች ተቀርጸውበት ነበር፥ የዘንባባውም ዛፎች ተቀርጸውበት ነበረ፥ የዘንባባውም ዛፍ ከኪሩብና ከኪሩብ መካከል ነበረ፥ ለእያንዳንዱም ኪሩብ ሁለት ፊት ነበረው።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 41:18
16 Referencias Cruzadas  

በእነዚሁ መደገፊያዎችና ጠፍጣፋ ነሐሶች መካከል ባለው ክፍት ቦታ ሁሉ በኪሩቤል፥ በአንበሶችና በዘንባባ ዛፎች አምሳል በተሠሩ ቅርጾች አጊጠው ነበር፤ እንዲሁም ዙሪያቸው የአበባ ጉንጉን በሚመስሉ ቅርጾች አጊጠው ነበር።


ጓዳዎቹም በበሩ ውስጥ በዙሪያው በነበሩትም በግንቡ አዕማድ ትናንሽ መስኮቶች ነበሩአቸው፤ ደግሞም በመተላለፊያው ውስጥ በዙሪያው መስኮቶች ነበሩ፤ በግንቡም አዕማድ ሁሉ ላይ የዘንባባ ዛፍ ተቀርጾባቸው ነበር።


መስኮቶቹ፥ መተላለፊያዎቹና የዘንባባ ዛፎቹ ወደ ምሥራቅ በሚመለከተው በር ካሉት ጋር መጠናቸው እኩል ነበር። ወደ እርሱ የሚያደርሱ ሰባት ደረጃዎች አሉ፤ መተላለፊያዎቹም በፊት ለፊቱ ነበሩ።


እያንዳንዱ አራት አራት ፊት፥ እያንዳንዱም አራት አራት ክንፍ ነበሩት፥ ከክንፎቻቸው ሥርም የሰው እጅ የሚመስል ነገር ነበረ።


ቤቱንም ሰረገሎቹንም መድረኮቹንም ግንቦቹንም ደጆቹንም በወርቅ ለበጠ በግንቦቹም ላይ ኪሩቤልን ቀረጸ።


ከዚህ በኋላ አየሁ፤ እነሆም ማንም ሊቆጥራቸው የማይችል እጅግ ብዙ ሰዎች ከሕዝብና ከነገድ ከወገንም ከቋንቋም ሁሉ ነበሩ፤ ነጭ ልብስም ለብሰው የዘንባባንም ዝንጣፊዎች በእጆቻቸው ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆሙ፤


በእነርሱም ላይ፥ በመቅደሱ በሮች ላይ በግንቡ ላይ እንደተቀረጸው ዓይነት ኪሩቤልና የዘንባባ ዛፎች ተቀርጸው ነበር፤ በውጭ ባለው መተላለፊያ ፊት ወፍራም እንጨት ነበረ።


ከመሬት አንሥቶ እስከ መግቢያው ድረስ ኪሩቤልና የዘንባባ ዛፎች ተቀርጸው ነበር። የመቅደሱም ግንብ እንደዚህ ነበረ።


እያንዳንዱም አራት አራት ፊት ነበሩት፥ አንደኛው ፊት የኪሩብ ፊት፥ ሁለተኛው ፊት የሰው ፊት፥ ሦስተኛው ፊት የአንበሳ ፊት፥ አራተኛውም ፊት የንስር ፊት ነበረ።


የፊታቸውም ምስል የሰው ፊት፥ አራቱም በቀኝ በኩል የአንበሳ ፊት፥ በግራ በኩል የላም ፊት ነበራቸው፥ አራቱም ደግሞ የንስር ፊት ነበራቸው።


ታላቁንም ቤት በጥድ እንጨት ከደነው፥ በጥሩም ወርቅ ለበጠው፤ የዘንባባና የሰንሰለት አምሳል ቀረጸበት።


እነርሱንም ሙሉ በሙሉ በወርቅ በተለበጡ በኪሩቤል፥ በዘንባባ ዛፎችና በፈኩ የአበባ ቅርጾች አስጌጣቸው።


ከበሩ በላይ እስከ ውስጠኛው ቤት ድረስ፥ በዙሪያውም የነበረው ግንብ ሁሉ ውጭውም ውስጡም ተለካ።


ልሙጥ በሆነው ነገርም ላይ በአንበሶች፥ በበሬዎችና በኪሩቤል አምሳል የተቀረጹ ምስሎች ነበሩ፤ ከአንበሶቹ፥ ከበሬዎቹና ከኪሩቤሉ ቅርጾች ራስጌና ግርጌ የአበባ ጉንጉን የሚመስሉ ቅርጾች ነበሩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios