በጓዳዎቹም ፊት በዚህ በኩል አንድ ክንድ በዚያም በኩል አንድ ክንድ የሆነ ዳርቻ ነበረ፤ ጓዳውም በዚህ በኩል ስድስት ክንድ በዚያም በኩል ስድስት ክንድ ነበረ።
ሕዝቅኤል 40:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከአንዱ ጓዳ ደርብ ጀምሮ እስከ ሌላው ደርብ ድረስ የበሩ ወርድ ሀያ አምስት ክንድ ሆነ፤ መዝጊያውና መዝጊያውም ትይዩ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ከዘብ ቤቱ የኋላ ግድግዳ ጀምሮ እስከ ሌላው ጫፍ ድረስ ያለውን የመግቢያ በር ለካ፤ ከአንዱ መከለያ ግድግዳ እስከ ሌላው መከለያ ግድግዳ ያለው ርቀት ሃያ ዐምስት ክንድ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያ በኋላ መግቢያውን ከአንዱ ማረፊያ ክፍል በስተጀርባ እስከ ሁለተኛው ማረፊያ ክፍል በስተጀርባ፥ ከግድግዳ እስከ ግድግዳ ድረስ ለክቶ ኻያ አምስት ክንድ ሆኖ ተገኘ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከአንዱም የዕቃ ቤት ደርብ ጀምሮ እስከ ሌላው ደርብ ድረስ የበሩን ወርድ ሃያ አምስት ክንድ አድርጎ ለካ፤ በሩና በሩም ትይዩ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከአንዱም የዘበኛ ጓዳ ደርብ ጀምሮ እስከ ሌላው ደርብ ድረስ የበሩን ወርድ ሀያ አምስት ክንድ አድርጎ ለካ፥ መዝጊያውና መዝጊያውም ትይዩ ነበረ። |
በጓዳዎቹም ፊት በዚህ በኩል አንድ ክንድ በዚያም በኩል አንድ ክንድ የሆነ ዳርቻ ነበረ፤ ጓዳውም በዚህ በኩል ስድስት ክንድ በዚያም በኩል ስድስት ክንድ ነበረ።
ጓዳዎቹም በዚህ በኩል ሦስት በዚያም በኩል ሦስት ነበሩ፤ የግንቡ አዕማድና መተላለፊያዎቹ እንደ ፊተኛው በር መጠናቸው እኩል ነበር፤ ርዝመቱ አምሳ ክንድ ወርዱም ሀያ አምስት ክንድ ነበር።