የምሥራቁ በር ጓዳዎች በዚህ በኩል ሦስት በዚያ በኩል ደግሞ ሦስት ነበሩ፥ ሦስቱም እኩል ስፋት ነበራቸው፤ የግንቡም አዕማድ ወርድ በዚህ በኩልና በዚያ በኩል እኩል ነበረ።
ሕዝቅኤል 40:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የበሩን መግቢያ ወርድ ዐሥር ክንድ፥ የበሩን ርዝመት ዐሥራ ሦስት ክንድ አድርጎ ለካ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የበሩን ስፋት ለካ፤ ወርዱ ዐሥር ክንድ፣ ርዝመቱም ዐሥራ ሦስት ክንድ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የበሩን መግቢያ ሲለካ ወርዱ ዐሥር ክንድ ርዝመቱ ደግሞ ዐሥራ ሦስት ክንድ ሆኖ አገኘው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የበሩንም መግቢያ ወርድ ዐሥር ክንድ፥ የበሩንም ርዝመት ዐሥራ ሦስት ክንድ አድርጎ ለካ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የበሩንም መግቢያ ወርድ አሥር ክንድ የበሩንም ርዝመት አሥራ ሦስት ክንድ አድርጎ ለካ። |
የምሥራቁ በር ጓዳዎች በዚህ በኩል ሦስት በዚያ በኩል ደግሞ ሦስት ነበሩ፥ ሦስቱም እኩል ስፋት ነበራቸው፤ የግንቡም አዕማድ ወርድ በዚህ በኩልና በዚያ በኩል እኩል ነበረ።
በጓዳዎቹም ፊት በዚህ በኩል አንድ ክንድ በዚያም በኩል አንድ ክንድ የሆነ ዳርቻ ነበረ፤ ጓዳውም በዚህ በኩል ስድስት ክንድ በዚያም በኩል ስድስት ክንድ ነበረ።