ሕዝቅኤል 38:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚያ ቀን ነገር ወደ ልብህ ይመጣል፥ ክፉ ሐሳብንም ታስባለህ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በዚያ ቀን ሐሳብ ወደ አእምሮህ ይመጣል፤ ክፋትንም ታውጠነጥናለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልዑል እግዚአብሔር ለጎግ የሚለው ይህ ነው፥ “ያ ዘመን ሲደርስ ሐሳብ ወደ አእምሮህ ይመጣል፤ ክፉ ዕቅድም ታቅዳለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በዚያ ቀን ነገር ወደ ልብህ ይገባል፥ ክፉ አሳብንም ታስባለህ፤ እንዲህም ትላለህ፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚያ ቀን ነገር ወደ ልብህ ይገባል፥ ክፉ አሳብንም ታስባለህ፥ |
የጌታም መንፈስ ወደቀብኝ እንዲህም አለኝ፦ ጌታ እንዲህ ይላል ብለህ ተናገር፦ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ይህን ነገር ተናግራችኋል፥ እኔ የልባችሁን ሐሳብ አውቃለሁና።
ጴጥሮስም “የጌታን መንፈስ ትፈታተኑ ዘንድ ስለምን ተስማማችሁ? እነሆ፥ ባልሽን የቀበሩት ሰዎች እግር በደጅ ነው፤ አንቺንም ያወጡሻል፤” አላት።
ስለዚህም፥ በጨለማ የተሰወረውን ወደ ብርሃን የሚያወጣ ደግሞም የልብን ምክር የሚገልጥ ጌታ እስኪመጣ ድረስ፥ ጊዜው ሳይደርስ አንዳች አትፍረዱ፤ በዚያን ጊዜም እያንዳንዱ ምስጋናው ከእግዚአብሔር ዘንድ ይሆናል።