ሕዝቅኤል 34:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በላያቸውም አንድ እረኛ አቆማለሁ እርሱም ያሰማራቸዋል፥ እርሱም ባርያዬ ዳዊት ነው፤ ያሰማራቸዋል እረኛም ይሆናቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእነርሱ ላይ አንድ እረኛ፣ ባሪያዬን ዳዊትን አቆማለሁ፤ እርሱም ያሰማራቸዋል፤ እረኛቸውም ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደ አገልጋዬ እንደ ዳዊት ያለ ንጉሥ እረኛ አድርጌ አስነሣላቸዋለሁ፤ እርሱም በእንክብካቤ ይጠብቃቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በላያቸውም አንድ እረኛ አቆማለሁ፤ እርሱም ያሰማራቸዋል፤ እርሱም ባሪያዬ ዳዊት ነው፤ እረኛም ይሆናቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በላያቸውም አንድ እረኛ አቆማለሁ እርሱም ያሰማራቸዋል፥ እርሱም ባሪያዬ ዳዊት ነው፥ ያሰማራቸዋል እረኛም ይሆናቸዋል። |
አለቃቸው ከእነርሱ ውስጥ አንዱ ይሆናል፥ ገዥአቸውም ከመካከላቸው ይወጣል፤ እኔ አቀርበዋለሁ እርሱም ይቀርበኛል፤ ይህስ ባይሆን ለነፍሱ ዋስትና ሰጥቶ ወደ እኔ ለመቅረብ የሚደፍር ማን ነው? ይላል ጌታ።
ከሕዝቦች አወጣቸዋለሁ፥ ከአገሮች እሰበስባቸዋለሁ፥ ወደ ገዛ አገራቸውም አመጣቸዋለሁ፤ በእስራኤል ተራሮች ላይ፥ በፈሳሾች አጠገብ፥ በምድሪቱም መኖሪያ በሚሆኑ ስፍራዎች ሁሉ አሰማራቸዋለሁ።
በምድሪቱ በእስራኤል ተራሮች ላይ አንድ ሕዝብ አደርጋቸዋለሁ፥ አንድ ንጉሥ ለሁሉም ንጉሥ ይሆናል፤ ዳግመኛ ሁለት ሕዝብ አይሆኑም፥ ከዚያ ወዲያም ሁለት መንግሥቶች ሆነው አይከፈሉም።
ከዚያም በኋላ የእስራኤል ልጆች ተመልሰው አምላካቸውን ጌታንና ንጉሣቸውን ዳዊትን ይፈልጋሉ፤ በኋለኛውም ዘመን ፈርተው ወደ ጌታና ወደ መልካምነቱ ይመጣሉ።
ሰይፍ ሆይ፥ ባልንጀራዬ በሆነው ሰው በእረኛዬ ላይ ንቃ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ፤ በጎቹም እንዲበተኑ እረኛውን ምታ፤ እጄንም በታናናሾች ላይ አዞራለሁ።
“እኔ ኢየሱስ በአብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ይህን እንዲመሰክርላችሁ መልአኬን ላክሁ። እኔ የዳዊት ሥርና ዘር ነኝ፤ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ።”
በዙፋኑ መካከል ያለው በጉ እረኛቸው ይሆናልና፤ ወደ ሕይወትም ውሃ ምንጭ ይመራቸዋልና፤ እግዚአብሔርም እንባዎችን ሁሉ ከዐይናቸው ያብሳል።”