ከእናንተም ዘንድ ዓመፀኞችንና የበደሉኝን እለያለሁ። ከኖሩባትም ምድር አወጣቸዋለሁ፥ ወደ እስራኤል ምድር ግን አይገቡም፥ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።
ሕዝቅኤል 34:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላቸዋል፦ እነሆ እኔ በወፈረ በግና በከሳ በግ መካከል እፈርዳለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላቸዋል፤ እነሆ እኔ ራሴ በሰባው በግና በከሳው በግ መካከል እፈርዳለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ስለዚህ እነሆ፥ እኔ ልዑል እግዚአብሔር በሰቡና በደካሞች በጎቼ መካከል እፈርዳለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላቸዋል፦ እነሆ እኔ በወፈሩት በጎችና በከሱት በጎች መካከል እፈርዳለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላቸዋል፦ እነሆ፥ እኔ በወፈሩት በጎችና በከሱት በጎች መካከል እፈርዳለሁ። |
ከእናንተም ዘንድ ዓመፀኞችንና የበደሉኝን እለያለሁ። ከኖሩባትም ምድር አወጣቸዋለሁ፥ ወደ እስራኤል ምድር ግን አይገቡም፥ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ በእረኞች ላይ ነኝ፥ መንጋዎቼን ከእጃቸው እፈልጋለሁ፥ መንጋዎቼን ከማሰማራት አስተዋቸዋለሁ። ከዚያም ወዲያ እረኞች ራሳቸውን አያስማሩም፤ በጎቼንም ከአፋቸው አድናለሁ፥ መብልም አይሆኑላቸውም።