ሕዝቅኤል 34:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መንጋዎቼ በእግራችሁ በረገጣችሁት ይሰማራሉ በእግራችሁም ያደፈረሳችሁትን ይጠጣሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መንጋዬ የረጋገጣችሁትን መመገብና በእግራችሁ ያደፈረሳችሁትን መጠጣት ይገባዋልን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህም ዐይነት ሌሎች በጎቼ እናንተ የረጋገጣችሁትን ሣር ለመብላትና እናንተ ያደፈረሳችሁትንም ውሃ ለመጠጣት ተገደዋል።’ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጎችም በእግራችሁ በረገጣችሁት ይሰማራሉ፤ በእግራችሁም ያደፈረሳችሁትን ይጠጣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጎቼም በእግራችሁ በረገጣችሁት ይሰማራሉ በእግራችሁም ያደፈረሳችሁትን ይጠጣሉ። |
ከአሕዛብም ዘንድ ባወጣኋችሁ ጊዜ ከተበተናችሁባትም አገር ሁሉ በሰበሰብኋችሁ ጊዜ እንደ ጣፋጭ ሽታ እቀበላችኋለሁ፥ በአሕዛብም ፊት እቀደስባችኋለሁ።
የቀረውን ማሰማርያችሁን በእግራችሁ የረገጣችሁት፥ በመልካሙ ማሰማርያ መሰማራታችሁ ባይበቃችሁ ነውን? የቀረውንስ ውኃ በእግራችሁ ያደፈረሳችሁት፥ ጥሩውን ውኃ መጠጣታችሁ ባይበቃችሁ ነውን?