ሕዝቅኤል 34:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እናንተም መንጋዬ ሆይ፥ እነሆ በበግና በበግ መካከል፥ በአውራ በግና በአውራ ፍየል መካከል እፈርዳለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘መንጋዬ ስለ ሆናችሁት ስለ እናንተ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በበግና በበግ መካከል፣ በአውራ በግና በአውራ ፍየል መካከል እፈርዳለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘ስለ እናንተ ስለ መንጋዎቼ በመልካም በጎችና በክፉ በጎች በአውራ በጎችና በፍየሎች መካከል እፈርዳለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እናንተም መንጋዬ ሆይ! እነሆ በበግና በበግ መካከል፥ በአውራ በግና በአውራ ፍየልም መካከል እፈርዳለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እናንተም መንጋዬ ሆይ፥ እነሆ፥ በበግና በበግ መካከል፥ በአውራ በግና በአውራ ፍየልም መካከል፥ እፈርዳለሁ። |
ቁጣዬ በእረኞች ላይ ነዷል፥ መሪዎችንም እቀጣለሁ፤ የሠራዊት ጌታም የይሁዳን ቤት መንጋውን ጐብኝቶአል፥ በውጊያ ላይ ክብር እንደተቀዳጀ ፈረስ ያደርጋቸዋል።
“እነሆ፥ እንደ ምድጃ እሳት የሚነድ ቀን ይመጣል፤ ትዕቢተኞች ሁሉና ኃጢአትን የሚሠሩ ሁሉ ገለባ ይሆናሉ፤ የሚመጣውም ቀን ያቃጥላቸዋል” ይላል የሠራዊት ጌታ፤ ሥርንና ቅርንጫፍንም አያስቀርላቸውም።