ሕዝቅኤል 33:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ አንተ እንደ ጥሩ ዘፈን፥ እንደ መልካም ድምፅ፥ እንደ ጎበዝ ተጫዋች ሆነህላቸዋል፤ ቃልህንም ይሰማሉ ነገር ግን አያደርጉትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቃልህን ሰምተው ሥራ ላይ የማያውሉት በመሆናቸው፣ አንተ ለእነርሱ በአማረ ድምፅ የፍቅር ዘፈን የሚዘፍን፣ በዜማ መሣሪያም አሳምሮ የሚጫወት ሙዚቀኛ ሆነህላቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ በእነርሱ ዘንድ ጥሩ ድምፅ እንዳለውና ደኅና አድርጎ የሙዚቃ መሣሪያን እንደሚጫወት እንደ ፍቅር ዘፈን አቀንቃኝ ነህ፤ አንተ የምትለውን ይሰማሉ እንጂ፤ አይፈጽሙትም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ አንተ መልካም ድምፅ እንዳለው እንደሚወደድ መዝሙር ማለፊያም አድርጎ በገና እንደሚጫወት ሰው ሁነህላቸዋል፤ ቃልህንም ይሰማሉ ነገር ግን አያደርጉትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ አንተ መልካም ድምፅ እንዳለው እንደሚወደድ መዝሙር ማለፊያም አድርጎ በገና እንደሚጫወት ሰው ሆነህላቸዋል፥ ቃልህንም ይሰማሉ ነገር ግን አያደርጉትም። |
ምክንያቱም ዮሐንስ ጻድቅና ቅዱስ ሰው መሆኑን ሄሮድስ በማወቁ ይፈራውና ይጠብቀው ነበር። ዮሐንስ የሚናገረውን ሲሰማ ሄሮድስ ቢታወክም በደስታ ያዳምጠው ነበር።