ሕዝቅኤል 33:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሠራው ኃጢአት ሁሉ አይታሰብበትም፤ ፍርድንና ቅን ነገርን አድርጎአል፥ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሠራው ኀጢአት አንዱም አይታሰብበትም፤ ቀናውንና ትክክለኛውን አድርጓልና፤ በርግጥ በሕይወት ይኖራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሠራውን ኃጢአት ሁሉ ይቅር እልለታለሁ፤ እውነተኛና ትክክለኛ የሆነውን ሥራ በመሥራቱ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሠራውም ኀጢአት ሁሉ አይታሰብበትም፤ ፍርድንና ቅን ነገርን አድርጎአልና፤ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሠራው ኃጢአት ሁሉ አይታሰብበትም፥ ፍርድንና ቅን ነገርን አድርጎአል፥ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል። |
ስጦታውም አንድ ሰው ኃጢአትን በማድረጉ እንዳመጣው ውጤት አይደለም፤ በአንድ በኩል፥ ፍርዱ የአንድን ሰው በደል ተከትሎ ኩነኔን አመጣ፤ በሌላ በኩል ግን ስጦታው ብዙ በደልን ተከትሎ ጽድቅን አመጣ።
ይህም የሆነው፥ ኃጢአት በሞት እንደ ነገሠ፥ እንዲሁ ደግሞ ጸጋ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ለዘለዓለም ሕይወት፥ በጽድቅ በኩል እንዲነግሥ ነው።