ሕዝቅኤል 31:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሕዝቦች መካከል በጥላው የኖሩ ክንዱ ወደነበሩት፥ በሰይፍ ወደ ተገደሉት ከእርሱ ጋር ወደ ሲኦል ወረዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከአሕዛብ መካከል ከርሱ ጋራ ያበሩ፣ በጥላው ሥር የኖሩ፣ በሰይፍ ከሞቱት ጋራ ለመቀላቀል ወደ መቃብር ወርደዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጥላው ሥር የነበሩትና ከሕዝቦች መካከል ተባባሪዎቹ የነበሩት በሰይፍ ወደ ተገደሉት ከእርሱ ጋር ወደ ሙታን ዓለም ይወርዳሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም በሰይፍ ወደ ተገደሉት ወደ ሲኦል ከእርሱ ጋር ወረዱ፤ በጥላው ሥር ይኖሩ የነበሩ ዘሮቹም በአሕዛብ መካከል ጠፉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ክንዱም ወደ ነበሩት በአሕዛብም መካከል በጥላው ወደ ተቀመጡት፥ በሰይፍ ወደ ተገደሉት ሰዎች ወደ ሲኦል ከእርሱ ጋር ወረዱ። |
ሲኦል በመምጣትህ ልትገናኝህ በታች ታወከች፤ የሞቱትንም፥ የምድርንም ታላላቆች ሁሉ፥ ለአንተ አንቀሳቀሰች፥ የአሕዛብንም ነገሥታት ሁሉ ከዙፋኖቻቸው አስነሣች።
ሬስ። ስለ እርሱ፦ በአሕዛብ መካከል በጥላው በሕይወት እንኖራለን ያልነው በእግዚአብሔር የተቀባ፥ የሕይወታችን እስትንፋስ፥ በጉድጓዳቸው ተያዘ።
ባዕዳን፥ የሕዝቦች ጨካኞች የሆኑ፥ ቆርጠው ጣሉት፤ በተራሮች እና በሸለቆዎች ሁሉ ውስጥ ቅርጫፎቹ ወደቁ፥ ቅርንጫፎቹም በምድር ፈሳሾች ሁሉ ላይ ተሰባበሩ፥ የምድርም ሕዝቦች ሁሉ ከጥላው ወጥተው ትተውት ሄዱ።
የሰማይ ወፎች ሁሉ ጎጆአቸውን በቅርንጫፎቹ ላይ ሠሩ፥ የምድር አራዊት ሁሉ ከቅርጫፎቹ በታች ወለዱ፥ ታላላቅ ሕዝቦች ሁሉ ከጥላው በታች ኖሩ።
በተዘራችም ጊዜ ትወጣለች፤ ከአትክልትም ሁሉ የምትበልጥ ትሆናለች፤ የሰማይ ወፎችም በጥላዋ ሊሰፍሩ እስኪችሉ ታላላቅ ቅርንጫፎች ታወጣለች።”