ሕዝቅኤል 30:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የግብጽ ምሽግ በሆነችው በሲን ላይ መዓቴን አፈስሳለሁ፤ የኖን ብዛት አጠፋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የግብጽ ምሽግ በሆነችው፣ በሲን ላይ መዓቴን አፈስሳለሁ፤ ስፍር ቍጥር የሌለውን የቴብስን ሕዝብ አጠፋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የግብጽ ዋና ምሽግ የሆነችው የፔሉስየም ከተማ የቊጣዬ መዓት እንዲወርድባት አደርጋለሁ፤ የቴብስን ብዙ ሕዝብ ሁሉ እገድላለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በግብፅም ኀይል በሲን ላይ መዓቴን አፈስሳለሁ፤ የሜምፎስንም ብዛት አጠፋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በግብጽም ምሽግ በሲን ላይ መዓቴን አፈስሳለሁ፥ የኖእንም ብዛት አጠፋለሁ። |
ከኤሊምም ተነሱ፥ የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ ከግብጽ ምድር ከወጡ በኋላ በሁለተኛው ወር፥ በዓሥራ አምስተኛው ቀን በኤሊምና በሲና መካከል ወዳለችው ወደ ሲን ምድረ በዳ መጡ።