ሕዝቅኤል 3:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንግግራቸው ጥልቅ ወደ ሆነ፥ ቋንቋቸውም ከባድ ወደ ሆነ፥ ቃላቸውንም መስማት ወደማይቻልህ ታላላቅ ሕዝቦች አልላክሁህም። ወደ እነርሱ ልኬህ ቢሆን ኖሮ ይሰሙህ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንግግራቸው ወደማይገባና ቋንቋቸው ወደማይታወቅ፣ ቃላቸውንም መረዳት ወደማይቻልህ ብዙ ሕዝብ አልላክሁህም። ወደ እነርሱ ልኬህ ቢሆን ኖሮ፣ በርግጥ ይሰሙህ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንግግራቸው ግራ የሚያጋባ፥ ቋንቋቸው ወደማይታወቅና የቃላቸውን ትርጒም ልታስተውለው ወደማትችል ታላላቅ ሕዝቦች ልኬህ ቢሆን ኖሮማ በሰሙህ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንግግራቸው ልዩ ወደ ሆነ፥ ቋንቋቸውም ሌላ ወደ ሆነ፥ ቃላቸውንም ታውቅ ዘንድ ወደማይቻልህ ሕዝብ አልላክሁህም። ወደ እነዚያስ ልኬህ ቢሆን ኖሮ በሰሙህ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንግግራቸው ወደ ጠለቀው ቋንቋቸውም ወደማይታወቅ ቃላቸውንም ታውቅ ዘንድ ወደማይቻልህ ሕዝብ አልላክሁህም። ወደ እነዚያስ ልኬህ ቢሆን ኖሮ በሰሙህ ነበር። |
ነገር ግን የእስራኤል ቤት እኔን መስማት እንቢ ብለዋልና አንተንም አይሰሙህም፥ ምክንያቱም የእስራኤል ቤት ሁሉ የጠነከረ ግምባርና የደነደነ ልብ አላቸውና።