ሕዝቅኤል 27:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአንቺ ውስጥ የነበሩ የጌባል ሽማግሌዎችና ጥበበኞችዋ ስብራትሽን ይጠግኑ ነበር፤ የባሕር መርከቦች ሁሉና መርከበኞቻቸው ከአንቺ ጋር ለመለዋወጥ በአንቺ ውስጥ ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጌባል ሽማግሌዎችና ባለሙያዎች፣ መርከብሽን ለመገጣጠም በመካከልሽ ነበሩ፤ የባሕር መርከቦችና መርከበኞቻቸው ሁሉ፣ ከአንቺ ጋራ ሊገበያዩ ይመጡ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የተበላሸውን ለመጠገን በጌባል ልምድ ያካበቱ ባለሙያዎች በአንቺ መካከል ነበሩ፤ መርከበኞች በመርከባቸው ወደ ወደብሽ እየመጡ ከአንቺ ጋር ይገበያዩ ነበር።’ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአንቺ ውስጥ የነበሩ የጌባል ሽማግሌዎችና ጥበበኞችዋ ስብራትሽን ይጠግኑ ነበር፤ ከአንቺም ጋር ይነግዱ ዘንድ የባሕር መርከቦች ሁሉና መርከበኞቻቸው በመካከልሽ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአንቺ ውስጥ የነበሩ የጌባል ሽማግሌዎችና ጥበበኞችዋ ስብራትሽን ይጠግኑ ነበር፥ ከአንቺም ጋር ይነግዱ ዘንድ የባሕር መርከቦች ሁሉና መርከበኞቻቸው በመካከልሽ ነበሩ። |
የጌባላውያንም ምድር፥ በፀሐይም መውጫ በኩል ከአርሞንዔም ተራራ በታች ካለችው በኣልጋድ ጀምሮ እስከ ሐማት መግቢያ ድረስ ያለችው ሊባኖስ ሁሉ፥
አሕዛብ ሁሉ ከዝሙትዋ ቁጣ ወይን ጠጅ ጠጥተዋልና፤ የምድርም ነገሥታት ከእርሷ ጋር ሴስነዋልና፤ የምድርም ነጋዴዎች ከቅምጥልነትዋ ኃይል የተነሣ ሀብታሞች ሆነዋልና፤” ብሎ ጮኸ።