በባሕር መግቢያ ለምትኖረውና፥ በብዙ ደሴቶች ላይ ከሚኖሩ ሕዝቦች ጋር ለምትነግደው ጢሮስ እንዲህ በላት፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጢሮስ ሆይ፥ አንቺ፦ “በውበት ፍጹም ነኝ” ብለሻል።
ሕዝቅኤል 27:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሸቀጥሽ ከባሕር በወጣ ጊዜ ብዙ ሕዝቦችን አጥግበሻል፤ በተትረፈረፈ በሀብትሽና በሸቀጣ ሸቀጥሽ የምድርን ነገሥታት አበልጽገሻል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሸቀጥሽ ከባሕር በወጣ ጊዜ፤ ብዙ ሕዝቦችን ታጠግቢ ነበር፣ በታላቅ ሀብትሽና ሸቀጥሽ፣ የምድርን ነገሥታት ታበለጥጊ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሸቀጥ ዕቃሽ በየሀገሩ ሲሠራጭ፥ የየሀገሩን ሕዝብ ፍላጎት ያሟላ ነበር፤ ከአንቺ በተትረፈረፈ ሀብትና ሸቀጥ የምድር ነገሥታትን አበልጽገሻል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በባሕር ውስጥ ምን ያህል ዋጋ ታገኚ ነበር? በብልጥግናሽ ብዛት ብዙ አሕዛብን አጠገብሽ፤ ከአንቺም ጋር አንድ ከሆኑት ለይተሽ የምድርን ነገሥታት ሁሉ ባለጸጎች አደረግሻቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሸቀጥሽ ከባሕር በወጣ ጊዜ ብዙ አሕዛብን አጥግበሻል፥ በብልጥግናሽና በንግድሽ ብዛት የምድርን ነገሥታት ባለ ጠጎች አድርገሻል። |
በባሕር መግቢያ ለምትኖረውና፥ በብዙ ደሴቶች ላይ ከሚኖሩ ሕዝቦች ጋር ለምትነግደው ጢሮስ እንዲህ በላት፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጢሮስ ሆይ፥ አንቺ፦ “በውበት ፍጹም ነኝ” ብለሻል።
በንግድህ ብዛት ግፍ በውስጥህ ተሞላ ኃጢአትንም ሠራህ፤ ስለዚህ እንደ ርኩስ ነገር ከእግዚአብሔር ተራራ ጣልሁህ፤ የምትጋርድ ኪሩብ ሆይ፥ ከእሳት ድንጋዮች መካከል አጠፋሁህ።
በራሳቸውም ላይ ትቢያ ነስንሰው እያለቀሱና እያዘኑ “በባሕር መርከቦች ያሉአቸውን ሁሉ ከሀብቷ የተነሣ ሀብታም ላደረገች ለታላቂቱ ከተማ ወዮላት! ወዮላት! በአንድ ሰዓት ጠፍታለችና፤” እያሉ ጮኹ።
አሕዛብ ሁሉ ከዝሙትዋ ቁጣ ወይን ጠጅ ጠጥተዋልና፤ የምድርም ነገሥታት ከእርሷ ጋር ሴስነዋልና፤ የምድርም ነጋዴዎች ከቅምጥልነትዋ ኃይል የተነሣ ሀብታሞች ሆነዋልና፤” ብሎ ጮኸ።