ሕዝቅኤል 27:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአርቫድ ልጆችና ሠራዊቶችሽ በቅጥሮችሽ ላይ ዙሪያውን ነበሩ፥ ጋማዳውያንም በግንቦችሽ ውስጥ ነበሩ፤ ጋሻቸውንም በቅጥርሽ ዙሪያ ሰቀሉ፥ ውበትሽንም ፍጹም አደረጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአራድና የሔሌክ ሰዎች፣ ቅጥርሽን በየአቅጣጫው ጠበቁ፤ የገማድ ሰዎችም፣ በምሽግሽ ውስጥ ነበሩ። ጋሻቸውንም በቅጥርሽ ዙሪያ ሰቀሉ፤ ውበትሽንም ፍጹም አደረጉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከአርዋድ የመጡ ወታደሮች የቅጽር ግንቦችሽን ይጠብቁ ነበር፤ ከጋማድም የመጡ ሰዎች ምሽጎችሽን ይጠብቁ ነበር፤ ጋሻዎቻቸውን በግንቦችሽ ላይ ሰቀሉ፤ የተዋብሽ እንድትሆኚ ያደረጉሽ እነርሱ ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአራድ ልጆችና ሠራዊቶችሽ በቅጥሮችሽ ላይ በዙሪያ ነበሩ፤ ገማዳውያንም በግንቦችሽ ውስጥ ነበሩ፤ የጦር መሣሪያቸውንም በዙሪያ በቅጥርሽ ላይ አንጠለጠሉ፤ ውበትሽንም ፈጽመዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአራድ ሰዎችና ሠራዊቶችሽ በቅጥሮችሽ ላይ በዙሪያ ነበሩ፥ ገማዳውያንም በግንቦችሽ ውስጥ ነበሩ፥ ጋሻቸውንም በዙሪያ በቅጥርሽ ላይ አንጠለጠሉ፥ ውበትሽንም ፈጽመዋል። |