ሕዝቅኤል 24:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የተመረጠውን መንጋ ውሰድ፥ አጥንቶቹም እንዲበስሉ ከስሩ ማገዶ ጨምር፤ በደንብ ይንተክተክ፥ አጥንቶቹም በውስጡ ይብሰሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከመንጋው ሙክቱን ውሰድ፤ ዐጥንቱን ለማብሰል ብዙ ማገዶ ከሥሩ ጨምር፤ ሙክክ እስከሚል ቀቅለው፤ ዐጥንቱም ይብሰል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከመንጋው መካከል ምርጥ በግ ውሰድና ዕረድ፤ ከድስቱም ሥር ማገዶ ጨምር፤ ሥጋውንና አጥንቱን እስኪበስል ድረስ ቀቅለው።’ ” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከመንጋው የተመረጠውን ውሰድ፤ አጥንቶቹም እንዲበስሉ በበታችዋ እሳት አንድድ፤ አፍላው፤ በእጅጉ ይፍላ፤ አጥንቶቹም በውስጥዋ ይቀቀሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከመንጋው የተመረጠውን ውሰድ፥ አጥንቶቹም እንዲበስሉ እንጨት በበታችዋ ማግድ፥ አጥንቶቹም በውስጥዋ ይቀቀሉ። |
ለደቡብም ዱር፦ የጌታን ቃል ስማ፤ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በአንተ ውስጥ እሳት አነድዳለሁ፤ በውስጥህም ያለውን የለመለመውንና የደረቀውን ዛፍ ሁሉ ይበላል፤ የሚቃጠል ነበልባል አይጠፋም፤ ከደቡብም ጀምሮ እስከ ሰሜን ድረስ ፊት ሁሉ ይቃጠልበታል።
አውሬውም ተያዘ፤ በእርሱም ፊት ተአምራትን እያደረገ የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትን ለምስሉም የሰገዱትን ያሳተ ሐሰተኛውም ነቢይ ከእርሱ ጋር ተያዘ፤ ሁለቱም በሕይወት ሳሉ በዲን ወደሚቃጠል ወደ እሳት ባሕር ተጣሉ።