ከሦስት ወር በኋላ፥ “ምራትህ ትዕማር ዘማዊ ሆናለች፤ ከዚህም የተነሣ አርግዛለች” ተብሎ ለይሁዳ ተነገረው። ይሁዳም፥ “አውጧትና በእሳት ተቃጥላ ትሙት” አለ።
ሕዝቅኤል 16:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አመንዝራነትሽ ከሌሎች ሴቶች የተለየ ነው፥ ማንም ለዝሙት የሚከተልሽ የለም፤ ማንም ዋጋ ሳይሰጥሽ አንቺ ዋጋ ትሰጫለሽ፤ የተለየሽም ሆንሽ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ያንቺ ግልሙትና ከሌሎቹ የተለየ ነው፤ ማመንዘር የሚሻ ማንም ሰው፣ አንቺን አሳድዶ ማግባባት አያስፈልገውም። ዋጋ ትከፍያለሽ እንጂ አይከፈልሽም፤ አንቺ የሌሎች ፍጹም ተቃራኒ ነሽ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም አንቺ ልዩ ዐይነት አመንዝራ ሴት ሆነሻል። ነገር ግን እንደዚህ እንድትሆኚ ያባበለሽ የለም፤ ገንዘብ ትከፍያቸዋለሽ እንጂ የሚከፍልሽ የለም፤ ስለዚህ በእርግጥ በአመንዝራነትሽ አንቺ ልዩ ነሽ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዝሙትሽ ከሌሎች ሴቶች ዝሙት ልዩ ነው፤ ማንም ለዝሙት የሚከተልሽ የለም፤ ዋጋ ሳይሰጥሽ አንቺ ዋጋ በመስጠትሽ በዚህ ነገር ልዩ ሆነሻል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ግልሙትናሽ ከሌሎች ሴቶች ግልብጥ ነው፥ ማንም ለግልሙትና የሚከተልሽ የለም፥ ዋጋ ሳይሰጥሽ አንቺ ዋጋ በመስጠትሽ በዚህ ነገር ልዩ ሆነሻል። |
ከሦስት ወር በኋላ፥ “ምራትህ ትዕማር ዘማዊ ሆናለች፤ ከዚህም የተነሣ አርግዛለች” ተብሎ ለይሁዳ ተነገረው። ይሁዳም፥ “አውጧትና በእሳት ተቃጥላ ትሙት” አለ።
ለአመንዝራዎች ሁሉ ሥጦታ ይሰጡአቸዋል፥ አንቺ ግን ለወዳጆችሽ ሁሉ ሥጦታሽን ትሰጫለሽ፥ ለአመንዝራነትሽ ከየአቅጣጫው ወደ አንቺ እንዲገቡ ጉቦ ትሰጫቸዋለሽ።