ዘፀአት 8:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንቁራሪቶቹን ከአንተ ከቤቶችህም ከአገልጋዮችህም ከሕዝብህም ያርቃል፤ በዓባይ ወንዝ ብቻ ይቀራሉ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሆኖም ግን አስማተኞቹ በድብቅ ጥበባቸው ተመሳሳይ ነገር ሠሩ፤ እነርሱም በግብጽ ምድር ላይ ጓጕንቸሮች እንዲወጡ አደረጉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን አስማተኞችም እንደዚሁ በአስማታቸው ተጠቅመው ጓጒንቸሮች በግብጽ ምድር ላይ እንዲመጡ አደረጉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የግብፅ ጠንቋዮችም በአስማታቸው እንዲህ አደረጉ፤ በግብፅም ሀገር ላይ ጓጕንቸሮችን አወጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጠንቍዮችም በአስማታቸው እንዲሁ አደረጉ፤ በግብፅም አገር ላይ ጓጕንቸሮችን አወጡ። |
በዚያን ቀን በምድር መካከል እኔ ጌታ እንደሆንሁ እንድታውቅ፥ የዝንብ መንጋ በእርሷ ላይ እንዳይሆን፥ ሕዝቤ የሚቀመጥባትን የጎሼንን ምድር እለያለሁ።
ኢያኔስና ኢያንበሬስም ሙሴን እንደ ተቃወሙት፥ እንዲሁ እነዚህ ደግሞ አእምሮአቸው የጠፋባቸው በእምነትም ረገድ ተፈትነው የወደቁ ሰዎች ሆነው እውነትን ይቃወማሉ።
በአውሬውም ፊት እንዲያደርግ ከተሰጡት ምልክቶች የተነሣ በምድር የሚኖሩትን ያስታል፤ የሰይፍም ቁስል ለነበረውና በሕይወት ለኖረው ለአውሬው ምስልን እንዲሠሩ በምድር የሚኖሩትን ያዛቸዋል።