ዘፀአት 8:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈርዖንም፦ “ለጌታ አምላካችሁ በምድረ በዳ እንድትሠዉ እለቅቃችኋለሁ፤ ነገር ግን ርቃችሁ አትሂዱ፥ ጸልዩልኝ” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም እንዲሁ አደረገ፤ አስጨናቂ የዝንብ መንጋ በፈርዖን ቤተ መንግሥትና በሹማምቱ ቤቶች ላይ ወረደ፤ መላው የግብጽ ምድር ከዝንቡ የተነሣ ተበላሽቶ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም የንጉሡ ቤተ መንግሥትና የመኳንንቱ ቤቶች ሁሉ በዝንብ መንጋ እንዲወረሩ አደረገ፤ መላዋም የግብጽ ምድር በዝንብ መንጋ ተበላሸች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም እንዲህ አደረገ፤ የውሻው ዝንብም በፈርዖን ቤት፥ በሹሞቹም ቤቶች ውሰጥ፥ በግብፅም ሀገር ሁሉ መጣ፤ ምድሪቱም ከውሻው ዝንብ የተነሣ ጠፋች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም እንዲሁ አደረገ፤ በፈርዖንም ቤት፥ በባሪያዎቹም ቤቶች ውስጥ ብዙ የዝንብ መንጋ መጣ፤ በግብፅም አገር ሁሉ ላይ ከዝንቡ መንጋ የተነሣ ምድር ጠፋች። |
ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን ጠርቶ “እንቁራሪቶቹን ከእኔና ከሕዝቤ እንዲያርቅ ወደ ጌታ ጸልዩልኝ፤ ለጌታም እንዲሠዋ ሕዝቡን እለቅቃለሁ” አላቸው።