La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፀአት 8:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ፈርዖንም እረፍት እንደሆነ ባየ ጊዜ ልቡን አደነደነ፤ ጌታም እንደ ተናገረ አልሰማቸውም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ጓጕንቸሮቹም ከአንተና ከቤቶችህ፣ ከሹማምትህና ከሕዝብህ ተወግደው በአባይ ወንዝ ብቻ ይወሰናሉ።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ጓጒንቸሮቹ ከአንተና ከቤትህ ሁሉ፥ ከመኳንንትህና ከሕዝብህም ሁሉ ዘንድ ይወገዳሉ፤ በዐባይ ወንዝ ውስጥ ካልሆነ በቀር፥ በሌላ ቦታ አይገኙም።”

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ጓጕ​ን​ቸ​ሮ​ቹም ከአ​ንተ፥ ከቤ​ቶ​ች​ህም፥ ከመ​ን​ደ​ሮ​ች​ህም፥ ከሹ​ሞ​ች​ህም፥ ከሕ​ዝ​ብ​ህም ይሄ​ዳሉ፤ በወ​ን​ዙም ብቻ ይቀ​ራሉ” አለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ጓጕንቸሮቹም ከአንተ፥ ከቤቶችህም፥ ከባርያዎችህም፥ ከሕዝብህም ይሄዳሉ፤ በወንዙም ብቻ ይቀራሉ” አለ።

Ver Capítulo



ዘፀአት 8:11
7 Referencias Cruzadas  

ጌታም ሙሴን አለው፦ “ወደ ግብጽ ስትመለስ በእጅህ ያደረግሁትን ተአምራት ሁሉ ተመልከት በፈርዖንም ፊት ታደርጋቸዋለህ፤ እኔም ልቡን አጸናዋለሁ፥ ሕዝቡንም አይለቅቅም።


ልክ ጌታ እንደ ተናገረው የፈርዖን ልብ ጸና፥ አልሰማቸውምም።


ጌታም ሙሴን አለው፦ “የፈርዖን ልብ ደነደነ፥ ሕዝቡንም አልለቅም አለ።


ጌታም ሙሴን አለው፦ “አሮንን ‘በትርህን ዘርጋ፥ በግብጽ ምድር ሁሉ ተናካሽ ትንኝ እንዲሆን የምድሩን ትቢያ ምታ በለው።’”


እንዲሁም አደረጉ፤ አሮንም እጁን ዘረጋ፥ በበትሩም የምድሩን ትቢያ መታ፥ በሰውና በእንስሳም ላይ ተናካሽ ትንኝ ሆነ፤ በግብጽ ምድር ያለ የምድር ትቢያ ሁሉ ተናካሽ ትንኝ ሆነ።


አስማተኞችም በአስማታቸው እንዲህ አደረጉ፥ በግብጽም ምድር ላይ እንቁራሪቶችን አወጡ።


ጌታም እንደ ሙሴ ቃል አደረገ፤ እንቁራሪቶቹም በየቤቶቹ፥ በየመንደሮቹና በሜዳም ሞቱ።