ዘፀአት 40:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ገበታውን ታስገባለህ፥ በአግባቡ ታሰናዳለህ፤ መቅረዙንም አስገብተህ ቀንዲሎቹን ትለኩሳለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠረጴዛውንም ወደ ውስጥ አምጥተህ ዕቃዎቹን በላዩ ላይ አሰናዳ፤ ከዚያም መቅረዙን አስገብተህ መብራቶቹን በቦታቸው አስቀምጥ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጠረጴዛውንም ወደ ውስጥ አስገብተህ የመገልገያ ዕቃዎችን በእርሱ ላይ አኑር፤ መቅረዙንም አስገብተህ መብራቶቹን በእርሱ ላይ አኑር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ገበታውንም ታገባለህ፤ በሥርዐቱም ታሰናዳዋለህ፤ መቅረዙንም አግብተህ ቀንዲሎቹን ትለኵሳለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ገበታውንም አግብተህ በእርሱ ላይ የሚኖረውን ዕቃ ታሰናዳለህ፤ መቅረዙንም አግብተህ ቀንዲሎቹን ትለኩሳለህ። |