ዘፀአት 38:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምሰሶዎቹ እግሮች ከነሐስ የተሠሩ፥ የምሰሶዎቹ ኩላቦችና ዘንጎች ከብር የተሠሩ ነበሩ፤ የምሰሶዎቹ ጉልላቶች በብር ተለብጠው ነበር፤ በአደባባዩ ያሉ ምሰሶዎች ሁሉ የብር ዘንጎች ነበሩአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምሰሶዎቹ መቆሚያዎች ንሓስ ነበሩ፤ ኵላቦቹና በምሰሶዎቹ ላይ ያሉት ዘንጎች ከብር የተሠሩ ነበሩ፤ ጫፎቻቸውም በብር ተለብጠው ነበር፤ ስለዚህ የአደባባዩ ምሰሶዎች ሁሉ የብር ዘንጎች ነበሯቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምሰሶዎቹ እግሮች የተሠሩት ከነሐስ ነበር፤ ኩላቦቹ ዘንጎቹና የምሰሶዎቹ ጫፎች መሸፈኛዎች ከብር የተሠሩ ነበሩ፤ በአደባባዩ ዙሪያ ያሉት ምሰሶዎች ሁሉ በብር ዘንጎች የተያያዙ ነበሩ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምሰሶዎቹም እግሮች የናስ፥ የምሰሶዎቹም ኵላቦችና ዘንጎች የብር ነበሩ፤ የምሰሶዎቹም ጕልላቶች በብር ተለብጠው ነበር፤ በአደባባዩ ላሉ ምሰሶዎች ሁሉ የብር ዘንጎች ነበሩአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የምሰሶቹም እግሮች የናስ፥ የምሰሶቹም ኩላቦችና ዘንጎች የብር ነበሩ፤ የምሰሶችም ጉልላቶች በብር ተለብጠው ነበር፤ በአደባባዩ ላሉ ምሰሶች ሁሉ የብር ዘንጎች ነበሩአቸው። |
የአደባባዩ መግቢያ መጋረጃ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይ ግምጃና ከጥሩ በፍታ የተጠለፈ ነበረ፤ ርዝመቱ ሀያ ክንድ፥ ቁመቱ እንደ አደባባዩ መጋረጃዎች አምስት ክንድ ነበረ፤
በዙሪያውም የሚቆሙትን የአደባባዩ ምሰሶች፥ እግሮቻቸውንም፥ ካስማዎቻቸውንም፥ አውታሮቻቸውንም፥ ዕቃዎቻቸውንና በተጓዳኝ የሚደረጉላቸውን አገልግሎቶች ሁሉ ነው፤ መሸከምም ያለባቸውን ዕቃዎች በየስሙ ትደለድላላችሁ።