“ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ግምጃ የተሠሩ ዐሥር መጋረጆች ያሉበትን ድንኳን ሥራ፤ ብልህ ሠራተኛ እንደሚሠራ ኪሩቤል በእነርሱ ላይ ይሁኑ።
ዘፀአት 36:35 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መጋረጃውንም ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይም ግምጃና ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ ሠራ፤ ብልህ ሠራተኛ እንደሠራው ኪሩቤልን በእርሱ ላይ አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና በቀጭኑ ከተፈተለ በፍታ፣ እጀ ጥበብ ባለሙያም ኪሩቤል የተጠለፉበት መጋረጃ ሠራ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መጋረጃዎችንም ከጥሩ በፍታ ሠሩ፤ እርሱም ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ከፈይ የተፈተለ ሲሆን የኪሩቤል ሥዕል ተጠልፎበት ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መጋረጃውንም ከሰማያዊና ከሐምራዊ፥ ከቀይም ግምጃ፥ ከተፈተለም ከጥሩ በፍታ አደረጉ፤ ኪሩቤልንም በጥልፍ ሥራ በእርሱ ላይ አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መጋረጃውንም ከሰማያዊና ከሐምራዊ ከቀይም ግምጃ፥ ከተፈተለም ከጥሩ በፍታ አደረጉ፤ ብልህ ሠራተኛ እንደሚሠራ ኪሩቤልን በእርሱ ላይ አደረጉ። |
“ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ግምጃ የተሠሩ ዐሥር መጋረጆች ያሉበትን ድንኳን ሥራ፤ ብልህ ሠራተኛ እንደሚሠራ ኪሩቤል በእነርሱ ላይ ይሁኑ።