ዘፀአት 36:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በማደሪያው በስተ ኋላ በምዕራብ በኩል ስድስት ሳንቃዎችን አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዳር በኩል ይኸውም በስተምዕራብ ጫፍ ባለው ማደሪያው ድንኳን ስድስት ወጋግራዎችን ሠሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከድንኳኑ በስተጀርባ በምዕራብ በኩል ስድስት ተራዳዎችን አደረጉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለድንኳኑም በምዕራቡ ወገን በስተኋላ ስድስት ሳንቆች አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለማደሪያውም በምዕራቡ ወገን በስተ ኋላ ስድስት ሳንቆች አደረጉ። |
በማደሪያውም በሁለተኛው ወገን ላሉት ሳንቃዎች አምስት መወርወሪያዎች፥ በማደሪያውም በስተ ኋላ በምዕራብ ወገን ላሉት ሳንቃዎች አምስት መወርወሪያዎች አድርግ።