የእያንዳንዱ መጋረጃ ርዝመት ሠላሳ ክንድ፥ የእያንዳንዱም መጋረጃ ወርድ አራት ክንድ ነበረ፤ የዐሥራ አንዱም መጋረጃዎች መጠን እኩል ነበረ።
ዘፀአት 36:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አምስቱን መጋረጃዎች አንድ ላይ ለብቻ፥ ስድስቱንም መጋረጃዎች አንድ ላይ ለብቻ አድርጎ አጋጠማቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐምስቱን መጋረጃዎች በአንድ በኩል፣ ሌሎቹን ስድስት መጋረጃዎች ደግሞ በሌላ በኩል አንድ ላይ አያያዟቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምስቱን በአንድ በኩል፥ ስድስቱንም በሌላ በኩል በማድረግ አገጣጥመው ሰፉአቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምስቱንም መጋረጃዎች እርስ በርሳቸው አንድ አደረጉ፤ ስድስቱንም መጋረጃዎች አንድ አድርገው አጋጠሙአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምስቱንም መጋረጆች እርስ በርሳቸው አንድ አድርገው፥ ስድስቱንም መጋረጆች አንድ አድርገው አጋጠሙአቸው። |
የእያንዳንዱ መጋረጃ ርዝመት ሠላሳ ክንድ፥ የእያንዳንዱም መጋረጃ ወርድ አራት ክንድ ነበረ፤ የዐሥራ አንዱም መጋረጃዎች መጠን እኩል ነበረ።
ከተጋጠሙት መጋረጃዎች በአንደኛው መጋረጃ ጠርዝ ላይ አምሳ ቀለበቶች አደረገ፤ እንዲሁም በሁለተኛው መጋረጃ ጠርዝ በሚጋጠሙበት በኩል አምሳ ቀለበቶች አደረገ።