ዘፀአት 35:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የብርና የነሐስ ስጦታ መስጠት የሚችል ሁሉ ለጌታ ስጦታ አቀረበ፤ የግራር እንጨት ያለው ሁሉ ለማንኛውም ሥራ አገልግሎት እንዲውል አመጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የብር ወይም የናስ መባ ማቅረብ የቻሉ ሁሉ ለእግዚአብሔር መባ አድርገው አመጡ፤ የግራር ዕንጨት ያለው ሁሉ አስፈላጊ በሆነው ሥራ እንዲውል አመጣው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብር ወይም ነሐስ ለማቅረብ ችሎታ ያላቸውም ሁሉ ስጦታቸውን ለእግዚአብሔር አመጡ፤ ለማንኛውም አገልግሎት የሚውል የግራር እንጨት ያለውም አመጣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስዕለት የተሳለ ሁሉ፥ የብርንም፥ የናስንም ስጦታ ለእግዚአብሔር ቍርባን አቀረበ፤ የማይነቅዝ ዕንጨት ያለው ሁሉ ለድንኳኑ ማገልገያ ለሚያስፈልገው ሥራ አመጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስእለት የተሳለ ሁሉ የብርንም የናስንም ስጦታ ለእግዚአብሔር ቁርባን አቀረበ፤ የግራርም እንጨት ያለው ሁሉ ለማገልገያ ሥራ አመጣ። |