ሙሴ ድንኳኑን እየወሰደ ከሰፈሩ ራቅ አድርጎ ከሰፈር ውጭ ይተክለው ነበር፤ “የመገናኛ ድንኳን” ብሎ ጠራው። ጌታን የፈለገ ሁሉ ከሰፈር ውጭ ወዳለው ወደ መገናኛው ድንኳን ይወጣ ነበር።
ዘፀአት 33:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴ ወደ ድንኳኑ በሚሄድበት ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ይነሡ ነበር፥ እያንዳንዱም በድንኳኑ ደጃፍ ይቆምና ሙሴ ወደ ድንኳኑ እስኪገባ ድረስ ይመለከቱት ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴ ወደ ድንኳኑ በወጣ ጊዜ ሕዝቡ በመነሣት ወደ ድንኳኑ እስኪገባ ድረስ በየድንኳኖቻቸው ደጃፍ ላይ ቆመው ይጠባበቁ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴ ወደዚያ በሄደ ቊጥር ሕዝቡ በየድንኳናቸው ደጃፍ ቆመው ሙሴ ወደ ድንኳን እስኪገባ ድረስ ይመለከቱታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም ከሰፈር ውጭ ወደአለው ድንኳን በሄደ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ፥ እያንዳንዱም በድንኳኑ ደጃፍ እየጠበቀ ይቆም ነበር፤ ሙሴም ወደ ድንኳኑ እስኪገባ ድረስ ይመለከቱት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም ወደ ድንኳኑ በሄደ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ይነሡ ነበር፥ እያንዳንዱም በድንኳኑ ደጃፍ ይቆም ነበር፥ ሙሴም ወደ ድንኳኑ እስኪገባ ድረስ ይመለከቱት ነበር። |
ሙሴ ድንኳኑን እየወሰደ ከሰፈሩ ራቅ አድርጎ ከሰፈር ውጭ ይተክለው ነበር፤ “የመገናኛ ድንኳን” ብሎ ጠራው። ጌታን የፈለገ ሁሉ ከሰፈር ውጭ ወዳለው ወደ መገናኛው ድንኳን ይወጣ ነበር።
ከቆሬና ከዳታን ከአቤሮንም ማደሪያ ከዙሪያውም ሁሉ ርቀው ገለል አሉ፤ ዳታንና አቤሮንም ሚስቶቻቸውም ልጆቻቸውም ሕፃናቶቻቸውም ወጥተው በድንኳኖቻቸው ደጃፍ ቆሙ።