La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፀአት 30:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ብርጉድ አምስት መቶ ሰቅል በመቅደሱ ሰቅል ሚዛን መሠረት፥ አንድ የኢን መሥፈሪያ የወይራ ዘይት፥

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዐምስት መቶ ሰቅል ብርጕድ ውሰድ፤ ሁሉም እንደ መቅደሱ ሰቅልና አንድ የሂን መስፈሪያ የወይራ ዘይት ይሁን፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስድስት ኪሎ ግራም ብርጒድ ውሰድ ይህም ሁሉ በተቀደሰው ድንኳን በታወቀው ሚዛን ልክ ይሁን፤ በዚህም ላይ አራት ሊትር ዘይት ጨምርበትና፥

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ብር​ጉ​ድም አም​ስት መቶ ሰቅል እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን፥ የወ​ይራ ዘይ​ትም አንድ የኢን መስ​ፈ​ሪያ ትወ​ስ​ዳ​ለህ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ብርጕድም አምስት መቶ ሰቅል እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን፥ የወይራ ዘይትም አንድ የኢን መሥፈሪያ ትወስዳለህ።

Ver Capítulo



ዘፀአት 30:24
8 Referencias Cruzadas  

ጽድቅን ወደድህ ዓመፃንም ጠላህ፥ ስለዚህ ከባልንጀሮችህ ይልቅ እግዚአብሔር አምላክ የደስታ ዘይትን ቀባህ።


ከአንዱ ጠቦት ጋር አሥረኛ እጅ የኢፍ መስፈሪያ መልካም ዱቄት ከአራተኛ እጅ የኢን መስፈሪያ ተወቅጦ ከተጠለለ ዘይት ጋር የተለወሰ፥ ለመጠጥ ቁርባን የሚሆን ደግሞ አራተኛ እጅ የኢን መስፈሪያ የወይን ጠጅ ታቀርባለህ።


“ምርጥ የሆኑትን ቅመሞች ለራስህ ውሰድ፤ ፈሳሽ ከርቤ አምስት መቶ ሰቅል፥ ግማሽ ይኸውም ሁለት መቶ አምሳ ሰቅል የቀረፋ ቅመም፥ የጠጅ ሣርም እንዲሁ ሁለት መቶ አምሳ ሰቅል፥


በቀማሚ እንደሚቀመም ቅመም የተቀደሰ የቅባት ዘይት ታደርገዋለህ፤ የተቀደሰ የቅባት ዘይትም ይሆናል።


አንድ ሰቅል ሀያ ጌራህ ይሆናል፤ ሀያ ሰቅል፥ ሀያ አምስት ሰቅል እና ዐሥራ አምስት ሰቅል ሲጨመር፥ አንድ ምናን ይሁንላችሁ።


ትክክለኛም ሚዛን፥ ትክክለኛም መመዘኛ፥ ትክክለኛም የኢፍ መስፈሪያ፥ ትክክለኛም የኢን መስፈሪያ ይኑሩአችሁ፤ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ።


የኢንም መስፈሪያ አራተኛ እጅ የወይን ጠጅ ለመጠጥ ቁርባን ከሚቃጠል መሥዋዕት ወይም ከሌላ መሥዋዕት ጋር ለእያንዳንዱ ጠቦት ታዘጋጃለህ።


ለእያንዳንዱ አምስት ሰቅል ውሰድ፤ እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን ትወስዳለህ፤ ሰቅሉም ሀያ አቦሊ ነው።