ዘፀአት 29:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሮንና ልጆቹ የአውራውን በግ ሥጋና በሌማት ያለውን ቂጣ በመገናኛው ድንኳን በር ሆነው ይበሉታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሮንና ወንዶች ልጆቹ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ የአውራውን በግ ሥጋና በሌማት ያለውን ዳቦ ይብሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም ሥጋ በመሶብ ውስጥ ተርፎ ከቀረው ቂጣ ጋር በቅዱሱ ድንኳኔ ደጃፍ ሆነው ይብሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሮንና ልጆቹም የአውራውን በግ ሥጋ፥ በመሶብም ያለውን እንጀራ በምስክሩ ድንኳን በር ይበሉታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሮንና ልጆቹም የአውራውን በግ ሥጋ በሌማትም ያለውን እንጀራ በመገናኛው ድንኳን በር ይበሉታል። |
ሙሴም አሮንንና ልጆቹን እንዲህ አላቸው፦ “ሥጋውን በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ቀቅሉ፤ ከዚህም ጋር ‘አሮንና ልጆቹ ይበሉታል’ ብዬ እንዳዘዝሁ የቅድስናው መሥዋዕት እንጀራ ከሚቀመጥበት መሶብ ውስጥ ያለውን እንጀራ በዚያ ትበሉታላችሁ።