ዘፀአት 28:35 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአገልግሎት ጊዜ በአሮን ላይ ይሆናል፤ እርሱም እንዳይሞት ወደ መቅደሱ በጌታ ፊት ሲገባና ሲወጣ ድምፁ ይሰማል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሮንም በአገልግሎቱ ጊዜ ይህን መልበስ አለበት፤ በእግዚአብሔር ፊት ወደ መቅደሱ በገባና ከመቅደሱ ሲወጣ እንዳይሞት የሻኵራዎቹ ድምፅ ይሰማል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሮን በክህነት በሚያገለግልበት ጊዜ ይህን ቀሚስ ይልበስ፤ በተቀደሰው ስፍራ በፊቴ በተገኘ ጊዜ ወይም ከዚያ በሚወጣበት ጊዜ የመርገፉ ድምፅ ስለሚሰማ ከመሞት ይድናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በማገልገል ጊዜም በአሮን ላይ ይሆናል፤ እርሱም እንዳይሞት ወደ መቅደሱ በእግዚአብሔር ፊት ሲገባና ሲወጣ ድምፁ ይሰማል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በማገልገል ጊዜም በአሮን ላይ ይሆናል፤ እርሱም እንዳይሞት ወደ መቅደሱ በእግዚአብሔር ፊት ሲገባና ሲወጣ ድምፁ ይሰማል። |
ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እኔ በስርየቱ መክደኛ ላይ በደመናው ውስጥ እታያለሁና፥ እንዳይሞት በመጋረጃው ውስጥ በታቦቱ ላይ ወዳለው ወደ ስርየቱ መክደኛ ወደተቀደሰው ስፍራ፥ ሁልጊዜ እንዳይገባ ለወንድምህ ለአሮን ንገረው።