ዘፀአት 28:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለደረት ኪሱም ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ሥራ፥ ሁለቱንም ቀለበቶች በደረት ኪሱ በሁለቱ ጫፎች አድርጋቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለርሱም ሁለት የወርቅ ቀለበቶች አብጅተህ ከደረት ኪሱ ሁለት ጐኖች ጋራ አያይዘው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁለት የወርቅ ቀለበቶች ሠርተህ በደረት ኪሱ ከላይኛው ማእዘን በኩል እንዲጋጠሙ አድርግ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለልብሰ እንግድዓውም ሁለት የወርቅ ቀለበቶች ሥራ፤ ሁለቱንም ቀለበቶች በልብሰ እንግድዓው በሁለቱ ወገን አድርጋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለደረቱ ኪስም ሁለት የወርቅ ቀለበቶች ሥራ፥ ሁለቱንም ቀለበቶች በደረቱ ኪስ በሁለቱ ወገን አድርጋቸው። |