La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፀአት 28:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አራት ረድፍ የሆነ የዕንቁ ፈርጥ አድርግበት፤ በመጀመሪያው ረድፍ ሰርድዮን፥ ቶጳዝዮንና የሚያብረቀርቅ ዕንቁ፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም በላዩ ላይ በአራት ረድፍ የከበሩ ድንጋዮች አድርግበት፤ በመጀመሪያው ረድፍ ሰርድዮን፣ ቶጳዝዮን፣ የሚያበረቀርቅ ዕንቍ፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አራት ረድፍ የሆነ የዕንቊ ፈርጥ አድርግበት፤ በመጀመሪያው ረድፍ ሰርድዮን፥ ቶጳዝዮንና፥ የሚያብረቀርቅ ዕንቊ፥ 18

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በአ​ራት ተራ የሆነ የዕ​ንቍ ፈርጥ አድ​ር​ግ​በት፤ የድ​ን​ጋ​ዮ​ቹም ተራ ሰር​ድ​ዮን፥ ጳዝ​ዮን፥ መረ​ግድ ነው፤ ይህም መጀ​መ​ሪ​ያው ተራ ነው፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በአራት ተራ የሆነ የዕንቁ ፍርጥ አድርግበት፤ በፊተኛው ተራ ሰርድዮን፥ ቶጳዝዮን፥ የሚያብረቀርቅ ዕንቁ፤

Ver Capítulo



ዘፀአት 28:17
15 Referencias Cruzadas  

በቅርጽ ሠራተኛ ሥራ እንደ ማኅተም ቅርጽ አድርገህ የእስራኤልን ልጆች ስም በሁለት ድንጋዮች ቅረጽ በወርቅ ፈርጥ ሥራቸው።


ርዝመቱ ስንዝር ስፋቱም ስንዝር ሆኖ አራት መዕዘንና ድርብ ይሁን።


በሁለተኛው ረድፍ በሉር፥ ሰንፔርና አልማዝ፤


ሁለት የመረግድ ድንጋይ ወስደህ የእስራኤልን ልጆች ስም ቅረጽባቸው፤


ወርቅና ብዙ ቀይ ዕንቁ ይገኛል፥ የእውቀት ከንፈር ግን የከበረች ጌጥ ናት።


ከውድ ዕንቁም ትከብራለች፥ ከምትመኘው ነገር አንዳችም አይተካከላትም።


ልባም ሴትን ማን ሊያገኛት ይችላል? ዋጋዋ ከቀይ ዕንቁ እጅግ ይበልጣል።


ጥበብ ከዕንቁ ትበልጣለችና የከበረ ነገር ሁሉ አይተካከላትም።


ዛይ። አለቆችዋ ከበረዶ ይልቅ ጥሩ፥ ከወተት ይልቅ ነጭ ነበሩ፥ ገላቸው ከቀይ ዕንቁ ይልቅ ቀይ ነበረ፥ መልካቸውም እንደ ሰንፔር ነበረ።


በእግዚአብሔር የአትክልት ቦታ በዔድን ነበርህ፤ የከበረ ድንጋይ ሁሉ ልብስህ ነበር፥ ያቁት፥ ቶጳዝዮን፥ አልማዝ፥ ቢረሌ፥ መረግድ፥ ኢያስጲድ፥ ሰንፔር፥ በሉር፥ የሚያብረቀርቅ ዕንቁ፥ ወርቅ፥ ልብስህ ነበረ፤ የከበሮህና የእንቢልታህ ሥራ በአንተ ዘንድ ነበረ፤ በተፈጠርህበት ቀን ተዘጋጅተው ነበር።


እነርሱ የእኔ ይሆናሉ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ፤ እኔ በምሠራበት ቀን፥ ሰው የሚያገለግለውን ልጁን እንደሚምር፥ እንዲሁ እምራቸዋለሁ።