ዘፀአት 27:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሌላውም በኩል የመጋረዎቹ ርዝመት ዐሥራ አምስት ክንድ፥ ምሰሶዎቹ ሦስት፥ እግሮቹም ሦስት ይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሦስት ምሰሶዎች ሦስት መቆሚያዎች ያሏቸው ርዝመታቸው ዐሥራ ዐምስት ክንድ የሆነ መጋረጃዎች በሌላው በኩል ይሁኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሌላው በኩል ያለውም መጋረጃ እንደዚሁ ይሁን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሌላውም ወገን የመጋረጃዎቹ ርዝመት ዐሥራ አምስት ክንድ ይሆናል፤ ምሰሶዎቹም ሦስት፥ እግሮቹም ሦስት ይሁኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሌላውም ወገን የመጋረጆች ርዝመት አሥራ አምስት ክንድ ይሆናል፤ ምሰሶቹም ሦስት፥ እግሮቹም ሦስት ይሁኑ። |
ለአደባባዩም መግቢያ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይ ግምጃና ከጥሩ በፍታ በጥልፍ የተጠለፈ ሀያ ክንድ መጋረጃ ይሁን፤ ምሰሶዎቹ አራት፥ እግሮቹም አራት ይሁኑ።