እንዲሁም በሰሜን በኩል መቶ ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች፥ ከነሐስ የተሠሩ ሀያ ምሰሶዎች እና ሀያ እግሮች ይሁኑ፥ ለምሰሶዎቹ ኩላቦችና ዘንጎች የብር ይሁኑ።
ዘፀአት 27:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሀያ ምሰሶዎቹና ሀያ እግሮቹ ከነሐስ የተሠሩ ይሁኑ፤ የምሶሶቹ ኩላቦችና ዘንጎች ከብር የተሠሩ ይሁኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሃያ ምሰሶዎች፣ ሃያ የንሓስ መቆሚያዎች፣ የብር ኵላቦችና በምሰሶዎቹም ላይ ዘንጎች ይኑሩት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለእርሱም መደገፊያ ኻያ የነሐስ እግሮች ያላቸው ኻያ ምሰሶዎች ሥራ፤ በእነርሱም ላይ ከብር የተሠሩ ዘንጎችና ኩላቦች ይኑሩ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከናስ የተሠሩ ሃያ ምሰሶዎችና ሃያ እግሮች ይሁኑለት፤ የምሰሶዎቹም ኩላቦችና ዘንጎች የብር ይሁኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከናስ የተሠሩ ሀያ ምሰሶችና ሀያ እግሮች ይሁኑለት፤ የምሶሶቹም ኩላቦችና ዘንጎች የብር ይሁኑ። |
እንዲሁም በሰሜን በኩል መቶ ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች፥ ከነሐስ የተሠሩ ሀያ ምሰሶዎች እና ሀያ እግሮች ይሁኑ፥ ለምሰሶዎቹ ኩላቦችና ዘንጎች የብር ይሁኑ።
በአደባባዩ ዙሪያ ያሉትን እግሮች፥ የአደባባዩን መግቢያ እግሮች፥ የማደሪያውን ካስማዎች ሁሉና በአደባባዩ ዙሪያ ያሉትን ካስማዎች ሁሉ ሠራ።
እነዚህም ዓምዶች፥ የአንዱ ዓምድ ቁመት ዐሥራ ስምንት ክንድ ነበረ፥ የዙሪያውም ልኬት ዐሥራ ሁለት ክንድ ነበረ፤ ውፍረቱም አራት የጣት ስንዝር ያህል ነበረ፥ መሀል ለመሀልም ክፍት ነበረ።