ዘፀአት 26:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከታችም እስከ ላይ እስከ አንደኛው ቀለበት ድረስ አንዱ ሳንቃ ድርብ ይሁን፤ እንዲሁም ለሁለቱ ይሁን፤ እነርሱም ለሁለቱ ማዕዘን ይሆናሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእነዚህ ሁለት ማእዘኖች ላይ ከታች እስከ ላይ ድረስ ድርብ ሲሆኑ፣ በአንድ ቀለበት ውስጥ የሚገጥሙ መሆን አለባቸው፤ በሁለቱም ወገን እንዲሁ መሆን አለበት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህ በማእዘኖቹ ላይ ያሉት ተራዳዎች ከታች በኩል ተጣምረው እስከ ላይ አንደኛው ዋልታ መያያዝ አለባቸው፤ ሁለቱን ማእዘኖች የሚያገናኙት ሁለት ተራዳዎች በዚሁ ዐይነት ይሠሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከታችም እኩል ይሁኑ፤ ከላይ እስከ አንደኛው መጋጠሚያ ድረስ እንደ አንደኛ ክፍል እኩል ይሁኑ፤ እንዲሁም ለሁለቱ ማዕዘን አድርግ፤ እኩልም ይሁኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከታችም እስከ ላይ እስከ አንደኛው ቀለበት ድረስ አንዱ ሳንቃ ድርብ ይሁን፤ እንዲሁም ለሁለቱ ይሁን፤ እነርሱም ለሁለቱ ማዕዘን ይሆናሉ። |
ነገር ግን ወንድሞች ሆይ! ሁላችሁ ተስማምታችሁ በአንድ ልቡና እና በአንድ አቋም በአንድነት የተባበራችሁ እንድትሆኑ እንጂ መለያየት በመካከላችሁ እንዳይሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እለምናችኋለሁ።
እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ለማቅረብ፥ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ፥ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።