በአውሬ ተበልቶ ከሆነ የቀረውን ለምስክርነት ያምጣው፤ በአውሬም ስለተበላ አይክፈል።
እንስሳው ከጎረቤት ተሰርቆ ከሆነ ግን፣ ለባለቤቱ ካሳ መክፈል አለበት።
እንስሳው የተሰረቀ ከሆነ ግን ለባለቤቱ ይመለስለት፤
ከእርሱም ዘንድ ቢሰረቅ ለባለቤቱ ይክፈል።
ከእርሱም ዘንድ ቢሰረቅ የጠፋውን ያህል ለባለቤቱ ይመልስ።
አውሬ የሰበረውን አላመጣሁልህም ነበር፥ እኔው ራሴ ስለ እርሱ እከፍልህ ነበርሁ፥ በቀን ሆነ በሌሊት ቢሰረቅ፥ ያን ከእጄ ትፈልግ ነበር።
ከእርሱ ከተሰረቀ ግን ለባለቤቱ ይክፈል።
አንድ ሰው ከባልንጀራው አንዳች ቢዋስ ባለቤቱም ከእርሱ ጋር ሳይኖር ቢጎዳ፥ ወይም ቢሞት፥ ካሳ ይክፈለው።
ሌባው ግን ባይገኝ፥ እጁን በባልንጀራው ንብረት ላይ እንዳልዘረጋ እንዲታወቅ ባለቤቱ ወደ እግዚአብሔር ፊት ይቅረብ።