ዘፀአት 20:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም እነዚህን ቃሎች ሁሉ እንዲህ ሲል ተናገረ፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር እነዚህን ቃሎች ሁሉ እንዲህ ብሎ ተናገረ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እነዚህን ትእዛዞች ሁሉ ለሕዝቡ ተናገረ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ይህን ቃል ሁሉ እንዲህ ብሎ ተናገረ፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ይህን ቃል ሁሉ እንዲህ ብሎ ተናገረ፦ |
ይህ ሰው በሲና ተራራ ከተናገረው መልአክና ከአባቶቻችን ጋር በምድረ በዳ በማኅበሩ ውስጥ የነበረው ነው፤ ይሰጠንም ዘንድ ሕይወት ያላቸውን ቃላት ተቀበለ፤
ዐሥርቱን ቃላት ጌታ በተራራው ላይ በእሳት ውስጥ ሆኖ ሲናገራችሁ ተሰብስባችሁበት በነበረበት ቀን፥ ቀድሞ ተጽፈው እንደነበረው በጽላቶቹ ላይ ጻፈ፥ እነርሱንም ጌታ ለእኔ ሰጠኝ።
“እነዚህን ቃሎች ጌታ በተራራው ላይ ለጉባኤአችሁ ሁሉ በእሳትና በደመና፥ በድቅድቅ ጨለማው ውስጥ ሆኖ፥ በታላቅ ድምፅ ተናገረ፥ ምንም ምን አልጨመረም። በሁለቱም የድንጋይ ጽላቶች ላይ ጻፋቸው፥ ለእኔም ሰጠኝ።