ዘፀአት 18:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህንም ብታደርግና፥ እግዚአብሔር ቢያዝዝህ፥ መቋቋም ትችላለህ፥ ደግሞም ይህ ሕዝብ ሁሉ በሰላም ወደ ስፍራው በሰላም ይሄዳል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተ ይህን ብታደርግና እግዚአብሔርም ይህንኑ ቢያዝዝህ፣ ድካምህን መቋቋም ትችላለህ፤ እነዚህም ሰዎች ሁሉ ረክተው ወደ ቤታቸው ይሄዳሉ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ዐይነት ብትሠራና ይህም የእግዚአብሔር ፈቃድ ቢሆን ራስህን በከንቱ አታደክምም፤ ሕዝቡም በቀላሉ ጉዳዩ እየተፈጸመለት ወደየቤቱ ይሄዳል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህንም ቃሌን ብታደርግ፥ እግዚአብሔር ያበረታሃል፤ መፍረድም ትችላለህ፤ ሕዝቡም ሁሉ በሰላም ወደ ስፍራው ይመለሳል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህንም ብታደርግ፥ እግዚአብሔር እንዲሁ ቢያዝዝህ፥ መቆም ይቻልሃል፥ ደግሞም ይህ ሕዝብ ሁሉ በሰላም ወደ ስፍራው ይደርሳል። |
ሰዎቹ ግን፥ “አንተ መውጣት የለብህም፤ እንድንሸሽ ብንገደድ፥ ስለኛ ምንም አይገዳቸውም፤ ግማሾቻችን እንኳ ብንሞት፥ ስለኛ ምንም አይገዳቸውም፤ አንተ ግን ብቻህን ከእኛ ከዐሥሩ ሺህ ትበልጣለህ! ስለዚህ በከተማ ሆነህ ብትረዳን ይሻላል” አሉት።
ንጉሡም፥ “ኪምሃም ከእኔ ጋር ይሻገራል፤ አንተን ደስ የሚያሰኝህንም ሁሉ አደርግለታለሁ፤ ከእኔ የምትፈልገውን ማናቸውንም ነገር ለአንተም አደርግልሃለሁ” አለው።
የጽሩያ ልጅ አቢሳ ግን ዳዊትን ለመታደግ መጣ፤ ፍልስጥኤማዊውንም መትቶ ገደለው። ከዚያም የዳዊት ሰዎች፥ “የእስራኤል መብራት እንዳይጠፋ ከእንግዲህ አንተ ከእኛ ጋር ወደ ጦርነት መውጣት የለብህም” ብለው ማሉለት።
ጌታ ሰንበትን እንደ ሰጣችሁ እዩ፤ ስለዚህ በስድስተኛው ቀን የሁለት ቀን ምግብ ሰጣችሁ፤ ሰው ሁሉ በስፍራው ይቀመጥ፤ በሰባተኛው ቀን ማንም ከስፍራው አይውጣ።”
በሕዝቡ ላይ ሁልጊዜ ይፍረዱ፤ ትልቁን ነገር ሁሉ ወደ አንተ ያምጡት፥ ትንሹንም ነገር ሁሉ እነርሱ ይፍረዱ፤ እነርሱም ከአንተ ጋር ሸክሙን ይሸከማሉ፥ ለአንተም ይቀልልሃል።
በእነርሱና በጳውሎስ በበርናባስም መካከል ብዙ ጥልና ክርክር በሆነ ጊዜ፥ ስለዚህ ክርክር ጳውሎና በርናባስ ከእነርሱም አንዳንዶች ሌሎች ሰዎች ወደ ሐዋርያት ወደ ሽማግሌዎችም ወደ ኢየሩሳሌም ይወጡ ዘንድ ተቆረጠ።
እንደ ተገለጠልኝም ወጣሁ፤ ምናልባትም በከንቱ እንዳልሮጥ ወይም ሮጬ እንዳልሆን፥ በአሕዛብ መካከል የምሰብከውን ወንጌል፥ በመሪነታቸው ለታወቁት ለብቻቸው አስታወቅኋቸው።