ዘፀአት 18:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተ ከአንተም ጋር ያለው ሕዝብ ትደክማላችሁ፤ ይህ ነገር ይከብድሃልና፤ አንተ ብቻህን ልታደርገው አትችልም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተና ወደ አንተ የሚመጡት እነዚህ ሰዎች የምታደርጉት ነገር ቢኖር ራሳችሁን ማድከም ነው፤ ሥራው ለአንተ ከባድ ሸክም ነው፤ ብቻህን ልትወጣው አትችልም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተን ራስህንም ሆነ ሕዝቡን በከንቱ ታደክማለህ፤ ብቻህን ሆነህ ይህን ሁሉ ለመሥራት ይከብድብሃል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ፥ ከአንተም ጋር ያለው ሕዝብ ትደክማላችሁ፤ ይህ ነገር ይከብድብሃል፤ አንተ ብቻህን ልታደርገው አትችልም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህ ነገር ይከብድብሃልና አንተ ከአንተም ጋር ያለው ሕዝብ ትደክማላችሁ፤ አንተ ብቻህን ልታደርገው አትችልም። |
እኔ ግን ስለ ነፍሳችሁ በብዙ ደስታ ገንዘቤን አወጣለሁ፤ ራሴን እንኳ እከፍላለሁ። ከመጠን ይልቅ ብወዳችሁ፥ የናንተ ፍቅር እንዴት ያንሳል?