La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፀአት 16:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ስድስት ቀን ትሰበስባላችሁ ሰባተኛው ቀን ግን ሰንበት ነው፤ በእርሱ አይኖርም።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስድስት ቀን ትሰበስቡታላችሁ፤ በሰባተኛው ቀን በሰንበት ዕለት ግን ምንም ነገር አይኖርም።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህ ስድስት ቀን በተከታታይ ይህን ምግብ ሰብስቡ፤ የዕረፍት ቀን በሆነው በሰባተኛው ቀን ግን ምንም ምግብ አይኖርም።”

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ስድ​ስት ቀን ልቀ​ሙት፤ ሰባ​ተ​ኛው ቀን ግን ሰን​በት ነው፤ በእ​ርሱ አይ​ገ​ኝም” አለ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ስድስት ቀን ልቀሙት ሰባተኛው ቀን ግን ሰንበት ነው፤ በእርሱ አይገኝም አለ።

Ver Capítulo



ዘፀአት 16:26
6 Referencias Cruzadas  

ሙሴም፦ “ዛሬ ብሉት፥ ዛሬ ለጌታ ሰንበት ነውና፤ ዛሬ በሜዳ አታገኙትም።


በሰባተኛውም ቀን ከሕዝቡ አንዳንድ ሰዎች ሊሰበስቡ ወጡ፥ ምንም አላገኙም።


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በውስጠኛው አደባባይ ፊቱ ወደ ምሥራቅ የሚመለከተው በር በስድስቱ የሥራ ቀኖች ይዘጋ፤ ነገር ግን በሰንበት ቀን ይከፈት እንዲሁም በወር መባቻ ቀን ይከፈት።


የምኵራብ አለቃው ግን ኢየሱስ በሰንበት ስለ ፈወሰ ተቈጥቶ ሕዝቡን “ሊሠራባቸው የሚገባ ስድስት ቀኖች አሉ፤ እንግዲህ በእነርሱ መጥታችሁ ተፈወሱ እንጂ በሰንበት አይሆንም፤” አለ።


ስድስት ቀን ሥራ፥ ሥራህንም ሁሉ አከናውን፥