የፋሲካውንም መሥዋዕት እንደ ሥርዓቱ በእሳት ጠበሱ፤ የተቀደሰውንም ቁርባን በምንቸትና በሰታቴ በድስትም ቀቀሉ፥ ለሕዝቡም ሁሉ በፍጥነት አደረሱ።
ዘፀአት 12:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጥሬውን ወይም በውኃ የበሰለውን አትብሉ፥ ነገር ግን ራሱ፥ ከእግሮቹና ከሆድ ዕቃው ጋር በእሳት የተጠበሰውን ብሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጥሬውን ሥጋ ወይም ቅቅሉን አትብሉ፤ ነገር ግን ጭንቅላቱን፣ እግሮቹንና ሆድ ዕቃውን በእሳት ላይ ጠብሳችሁ ብሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሥጋውም ጥሬውን ወይም ቅቅሉን አትብሉ፤ ራሱን፥ እግሮቹን የሆድ ዕቃውንም ጭምር በሙሉ ጠብሳችሁ ሥጋውን ብሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጥሬውንም፥ በውኃም የበሰለውን አትብሉ፤ ነገር ግን በእሳት የተጠበሰውን ራሱን፥ እግሩንና ሆድ ዕቃውን ብሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጥሬውን በውኃም የበሰለውን አትብሉ፤ ነገር ግን ከራሱ ከጭኑ ከሆድ ዕቃው ጋር በእሳት የተጠበሰውን ብሉት፤ |
የፋሲካውንም መሥዋዕት እንደ ሥርዓቱ በእሳት ጠበሱ፤ የተቀደሰውንም ቁርባን በምንቸትና በሰታቴ በድስትም ቀቀሉ፥ ለሕዝቡም ሁሉ በፍጥነት አደረሱ።
የሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ስብ ሁሉ፥ በጉበቱ ላይ ያለውን መረብ፥ ሁለቱን ኩላሊቶችና በላያቸው ያለውን ስብ ወስደህ በመሠዊያው ላይ ታቃጥላለህ።
የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን ግን በውኃ ያጥባል፤ ካህኑም የሚቃጠል መሥዋዕት፥ በእሳትም የሚቀርብ ቁርባን አድርጎ፥ በጌታ ዘንድ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን ሁሉንም በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል።