አብርሃምም ልጁን እስማኤልን፥ በቤቱም የተወለዱትን ሁሉ፥ በብሩም የገዛቸውን ሁሉ፥ ከአብርሃም ቤተሰብ ወንዶቹን ሁሉ ወሰደ፥ የቍልፈታቸውንም ሥጋ እግዚአብሔር እንዳለው በዚያው ቀን ገረዘ።
ዘፀአት 12:44 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በብር የተገዛ የማንም ባርያ ቢኖር ከተገረዘ በኋላ ከእርሱ ይብላ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በገንዘብ የገዛኸው ማንኛውም ባሪያ ከገረዝኸው በኋላ መብላት ይችላል፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባሪያ እንዲሆናችሁ በገንዘባችሁ የገዛችሁት ሰው ግን አስቀድማችሁ ከገረዛችሁት በኋላ መብላት ይችላል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አገልጋይ ወይም በብር የተገዛ ቢኖር ከተገረዘ በኋላ ያን ጊዜ ከእርሱ ይብላ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በብር የተገዛ ባሪያ ቢኖር ከተገረዘ በኋላ ከእርሱ ይብላ። |
አብርሃምም ልጁን እስማኤልን፥ በቤቱም የተወለዱትን ሁሉ፥ በብሩም የገዛቸውን ሁሉ፥ ከአብርሃም ቤተሰብ ወንዶቹን ሁሉ ወሰደ፥ የቍልፈታቸውንም ሥጋ እግዚአብሔር እንዳለው በዚያው ቀን ገረዘ።