ሰባት ቀን ያልቦካ ቂጣ ትበላላችሁ፤ በመጀመሪያው ቀን ከቤቶቻችሁ እርሾ ታስወግዳላችሁ፤ ከመጀመሪያውም ቀን አንሥቶ እስከ ሰባተኛው ቀን የቦካ የሚበላ ያቺ ነፍስ ከእስራኤል ተለይታ ትጥፋ።
ዘፀአት 12:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመጀመሪያው ወር ከወሩም በዓሥራ አራተኛው ቀን ምሽት እስከ ከወሩ ሀያ አንድ ቀን ምሽት ድረስ ያልቦካ ቂጣ ትበላላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከመጀመሪያው ወር ከዐሥራ አራተኛው ቀን ምሽት እስከ ሃያ አንደኛው ቀን ምሽት ድረስ ቂጣ ትበላላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከመጀመሪያው ወር ከዐሥራ አራተኛው ቀን ዋዜማ ምሽት ጀምሮ እስከ ኻያ አንደኛው ቀን ምሽት ድረስ ያልቦካ እንጀራ ትበላላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከመጀመሪያውም ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን ሠርክ ጀምራችሁ እስከዚሁ ወር ሃያ አንደኛ ቀን ሠርክ ድረስ ቂጣ ትበላላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመጀመሪያውም ወር በአሥራ አራተኛው ቀን በመሸ ጊዜ ከወሩም እስከ ሀያ አንድ ቀን በመሸ ጊዜ የቂጣ እንጀራ ትበላላችሁ። |
ሰባት ቀን ያልቦካ ቂጣ ትበላላችሁ፤ በመጀመሪያው ቀን ከቤቶቻችሁ እርሾ ታስወግዳላችሁ፤ ከመጀመሪያውም ቀን አንሥቶ እስከ ሰባተኛው ቀን የቦካ የሚበላ ያቺ ነፍስ ከእስራኤል ተለይታ ትጥፋ።