ንጉሥ ዳዊት በራሱና በሳኦል ልጅ በዮናታን መካከል በጌታ ፊት ስላደረጉት መሐላ ሲል የሳኦልን ልጅ፥ የዮናታንን ልጅ መፊቦሼትን ከሞት አተረፈ።
መክብብ 8:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ፦ በመለኮታዊ መሐላ መሠረት የንጉሥን ትእዛዝ ጠብቅ እልሃለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአምላክ ፊት መሐላ ስለ ፈጸምህ፣ የንጉሥን ትእዛዝ አክብር እልሃለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለንጉሡ እታዘዛለሁ ብለህ በመሐላ ለእግዚአብሔር ቃል ስለ ገባህ ለንጉሥ ታማኝ ሁን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልጄ ሆይ፥ የንጉሥን አፍ ጠብቅ፤ ለመሐላ ቃልም አትቸኩል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ፦ በእግዚአብሔር መሐላ ምክንያት የንጉሥን ትእዛዝ ጠብቅ እልሃለሁ። |
ንጉሥ ዳዊት በራሱና በሳኦል ልጅ በዮናታን መካከል በጌታ ፊት ስላደረጉት መሐላ ሲል የሳኦልን ልጅ፥ የዮናታንን ልጅ መፊቦሼትን ከሞት አተረፈ።
ሕዝቡ ወደ ጫካው በገባ ጊዜ፥ የማሩ ወለላ እየተንጠባጠበ ወደ ምድር መውረዱን አየ፤ ሆኖም መሓላውን ፈርቶ ስለ ነበር፥ እጁን ወደ አፉ የዘረጋ ማንም አልነበረም።