መክብብ 7:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰው የአላዋቂዎችን ዜማ ከሚሰማ ይልቅ የጠቢባንን ተግሣጽ መስማት ይሻለዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሞኞችን መዝሙር ከመስማት፣ የጠቢባንን ሰዎች ተግሣጽ መስማት ይሻላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሞኞችን ዘፈን ከመስማት የጥበበኞችን ተግሣጽ መስማት ይሻላል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሰው የሰነፎችን ዘፈን ከሚሰማ ይልቅ የጠቢባንን ተግሣጽ መስማት ይሻለዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰው የሰነፎችን ዜማ ከሚሰማ ይልቅ የጠቢባንን ተግሣጽ መስማት ይሻለዋል። |