መክብብ 4:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድካማቸው መልካም ዋጋ አለውና አንድ ብቻ ከመሆን ሁለት መሆን ይሻላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለሥራቸው መልካም ውጤት ስለሚያገኙ፣ ከአንድ፣ ሁለት መሆን ይሻላል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሥራቸው ውጤት መልካም ሊሆን ስለሚችል አንድ ብቻ ከመሆን ሁለት መሆን ይሻላል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድካማቸው መልካም ዋጋ አለውና አንድ ብቻ ከመሆን ሁለት መሆን ይሻላል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድካማቸው መልካም ዋጋ አለውና አንድ ብቻ ከመሆን ሁለት መሆን ይሻላል። |
አንድ ሰው ብቻውን ይኖራል፥ ማንም አብሮት የለም፥ ልጅም ሆነ ወንድም የለውም፥ ለድካሙም መጨረሻ የለውም፥ ዐይኖቹም ሳይቀሩ ሀብትን አይጠግቡም። እንግዲህ ለማን እደክማለሁ፥ ሰውነቴንስ መልካሙን ነገር ለምን እነፍጋታለሁ? ይላል። ይህም ደግሞ ከንቱ ነገር ክፉም ጥረት ነው።
ጌታም የይሁዳን ገዢ የሰላትያልን ልጅ የዘሩባቤልን መንፈስ፥ የታላቁን ካህን የኢዮሴዴቅን ልጅ የኢያሱን መንፈስና የቀሩትንም ሕዝብ ሁሉ መንፈስ አስነሣ፤ መጥተውም የአምላካቸውን የሠራዊትን ጌታ ቤት ሠሩ።