እኔም ጥበብን ዕብደትንና አለማወቅን ለመመርመር ወሰንኩ፥ በፊት የተደረገውን መድገም ካልሆነ በቀር፥ ከንጉሥ በኋላ የሚመጣው ሰው ምን ያደርጋል?
መክብብ 3:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁን ያለው በፊት ነበረ፥ የሚሆነውም በፊት ሆኖ ነበር፥ እግዚአብሔርም ያለፈውን መልሶ ይሻዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁን ያለው ከዚህ በፊት የነበረው ነው፤ ወደ ፊት የሚሆነውም ቀድሞ የነበረ ነው፤ አምላክም ያለፈውን መልሶ ይሻዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚሆነውና መሆን የሚችለው ነገር ሁሉ ያው ቀድሞ ተደርጎ የነበረው ነው፤ እግዚአብሔር ያንኑ ቀድሞ የፈጠረውን ነገር እንዲደጋገም ያደርጋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በፊት የተደረገው አሁን አለ። ይደረግ ዘንድ ያለውም እነሆ ተደርጓል፤ እግዚአብሔርም ያለፈውን መልሶ ይሻዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁን ያለው በፊት ነበረ፥ የሚሆነውም በፊት ሆኖ ነበር፥ እግዚአብሔርም ያለፈውን መልሶ ይሻዋል። |
እኔም ጥበብን ዕብደትንና አለማወቅን ለመመርመር ወሰንኩ፥ በፊት የተደረገውን መድገም ካልሆነ በቀር፥ ከንጉሥ በኋላ የሚመጣው ሰው ምን ያደርጋል?