መክብብ 10:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባርያዎች በፈረስ ላይ ሲቀመጡ መሳፍንትም እንደ ባርያዎች በምድር ላይ ሲሄዱ አየሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መሳፍንት እንደ ባሮች በእግራቸው ሲሄዱ፣ ባሮች ፈረስ ላይ ተቀምጠው አይቻለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መሳፍንት እንደ አገልጋዮች በእግራቸው ሲሄዱ፥ አገልጋዮች ግን በፈረስ ተቀምጠው ሲጓዙ አየሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አገልጋዮች በፈረስ ላይ ሲቀመጡ፥ መኳንንትም እንደ አገልጋዮች በምድር ላይ በእግራቸው ሲሄዱ አየሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባሪያዎች በፈረስ ላይ ሲቀመጡ መሳፍንትም እንደ ባሪያዎች በምድር ላይ ሲሄዱ አየሁ። |