መክብብ 10:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሥሽ የከበረ ልጅ የሆነ፥ ለብርታት እንጂ ለስካር ያይደለ በጊዜ የሚበሉ መኳንንት ያሉሽ፥ አንቺ አገር ሆይ፥ የተመሰገንሽ ነሽ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንቺ ንጉሥሽ ከተከበረው ዘር የሆነ፣ ለመስከር ሳይሆን ለብርታት፣ በተገቢው ጊዜ የሚበሉ መኳንንት ያሉሽ ምድር ሆይ፤ ብፁዕ ነሽ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጨዋነት ያደገ ንጉሥና ለስካር ሳይሆን ብርታትና ኀይል ለማግኘት ብቻ በተወሰነ ጊዜ የሚበሉና የሚጠጡ መሪዎች ያሉአት አገር የተባረከች ናት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሥሽ የጌታ ልጅ የሆነ፥ መኳንንቶችሽም ለብርታት በጊዜ የሚበሉ፥ የማያፍሩም፥ አንቺ ሀገር ሆይ፥ የተመሰገንሽ ነሽ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሥሽ የከበረ ልጅ የሆነ፥ ለብርታት እንጂ ለስካር ያይደለ በጊዜ የሚበሉ መኳንንት ያሉሽ፥ አንቺ አገር ሆይ፥ የተመሰገንሽ ነሽ። |
አለቃቸው ከእነርሱ ውስጥ አንዱ ይሆናል፥ ገዥአቸውም ከመካከላቸው ይወጣል፤ እኔ አቀርበዋለሁ እርሱም ይቀርበኛል፤ ይህስ ባይሆን ለነፍሱ ዋስትና ሰጥቶ ወደ እኔ ለመቅረብ የሚደፍር ማን ነው? ይላል ጌታ።
በብሩም ደስ ያለህን ሁሉ ማለትም በሬና በግ፥ የወይን ወይም የብርቱ መጠጥ ወይም የምትሻውን ሁሉ ግዛበት። ከዚያም አንተና ቤተሰብህ በጌታህ በእግዚአብሔር ፊት ትበላዋለህ፤ አንተና ቤተሰብህም ሐሤትም ታደርጋላችሁ።